ካልኩለስ02a HOQlc RUGvCc rA
የካልኩለስ መሰረታዊ እርግጥ ካልኩለስ የሂሳብ ትምህርት ክፍል ሲሆን ለውጥን ለማጥናት የሚጠቅም መሳሪያ ነው። የካልኩለስ ዋና ዋና ክፍሎች ጥግ (limit); ውድድር(derivative); ጥርቅም (integral) እና በመጨረሻም አዕላፍ ዝርዝር (infinite series) ሲሆኑ እነዚህ አራቱ ጽንሰ ሓሳቦች በሁለት ዋና ዋና የጥናት ክፍሎች ይከፈላሉ እነርሱም ሥነ ማወዳደር (differentiation) እና ሥነ ማጠራቀም(integration) ናቸው። ማውጫ 1 ታሪክ 1.1 የካልኩለስ መሰረት 2 መሪ ሃሳቦች 3 ጥግና ኢምንት 4 የውድድር ካልኩለስ 4.1 ፍጥነት እንደ ውድድር 4.2 ኩርባ እንደ ውድድር 4.3 የሌብኒዝ ምልክቶች 5 አጠራቃሚካልኩለስ 6 የካልኩለስ መሰረታዊ እርግጥ 6.1 የካልኩሊ ጥቅም 7 ማጣቀሻዎች 8 የውጭ መያያዣዎች 8.1 ኢንተርኔት ላይ ያሉ የእንግሊዝኛ መፃህፍት 8.2 ኢንተርኔት ድረ ገጾች ታሪክ [ ለማስተካከል | ኮድ አርም ] ካልኩለስ አዲስ የተገኘ የሂሳብ መሳሪያ ቢመስልም የጥንቶቹ ምሁራን ሳይቀር ጭላንጭሉን በማየት ግኝቶቻችቸውን ለታሪክ ትተው አልፈዋል። ከነዚህ ውስጥ የጥንታዊ ግብጽ ጸሃፍት ሳይጠቀሱ አይታለፉም። ለምሳሌ የሞስኮው ፓፒሪ ተብሎ በሚታወቀው ክርስቶስ ከመወለዱ 1820 አመታት በፊት የተጻፈው የግብጻውያን መዝገብ ላይ፣ የጥረዛ ካልኩለስ ጭላንጭልን እናገኛለን። በዚህ የጥንቱ ዘመን ጽሁፍ ላይ ደራሲው የቁና (እራሱ የተቆረጠ ሾጣጣን ) መጠነ ይዘት እንድናገኝ ጥያቄ ያቀርብና መልሱን በትክክል ያስቀምጣል። ይህን አይነት ጥያቄ በጥንታዊ ባቢሎናውያንም የተመዘገበ ቢሆንም መልሳቸው ግን ስህተት ነበር። በዚህ ምክንያት የጥንቶቹ ግብጻውያን የካልኩ...